Monday, October 2, 2023

በኮምፒውተራችን አዲስ ዊንዶው ምርት ከጫንን በኋላ እንዴት ደህንነቱን አስተማማኝ እናደርጋለን?

 


በኮምፒውተራችን አዲስ ዊንዶው ምርት ከጫንን በኋላ እንዴት ደህንነቱን አስተማማኝ እናደርጋለን?

አዲስ ዊንዶውስ ምርቶችን /Windows/ (7፣ 8፣10) ወይም ሌላ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ከጫንን በኋላ ደህንነቱ የተጠበቀ ለማድረግና ለማሻሻል ከዚህ በታች የተቀመጡትን የደህንነት እርምጃዎች መተግበር ይመከራል፡፡

1. የዊንዶው ስርዓትን ማዘመን/up to date/ የቅርብ ጊዜ የደህንነት ማዘመኛዎች እና መጠገኛዎችን /updates and patches/ መጫን፡፡

2. ሶፍትዌሮችን ማዘመን /Update software/ ፕሮግራሞች እና መተግበሪያዎች ሁሉም ዓይነት የቅርብ ጊዜ ማዘመኛዎች እና የደህንነት መጠገኛዎች መኖራቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ የታወቁ ሶፍትዌሮች እንደ ጃቫ ፣ አዶቤ ፍላሽ ፣ አዶቤ ሾክዌቭ ፣ አዶቤ አክሮባት ሪደር የመሳሰሉት ጊዜ ያለፈባቸው ከሆኑ በአጥፊ ተልእኮ ላይ የተሰማሩ ተዋንያን ሚስጥራዊ የሆኑ መረጃዎች በቀላሉ ለመድረስ ያስችላቸዋል።

3. መልሶ ማግኛ ስርዓት መፍጠር/Create a restore point/ ለዊንዶው ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች(OS) የደህንነት ማዘመኛዎች ከተጫነ ቀጣዩ እርምጃ በዊንዶውስ ውስጥ ወደ ነበረበት የመመለሻ ቦታ መፍጠር ነው። በኮምፒተር ላይ ችግርን ሊያስከትሉ የሚችሉ ወይም ስርዓቱ ላይ ማንኛቸውም ለውጦች ከማድረግዎ በፊት የመልሶ ማግኛ አማራጭን ተግባራዊ ማድረግ ይመከራል።

4. ፀረ-ቫይረስ መጫን Install antivirus product - አስተማማኝ የደህንነት መፍትሔ የሚሰጥ ማለትም ሪልታይም ቅኝት ፣ ራስ-ሰር ዝመና (Automatic update) እና ፋየርዎል ማካተት አለበት

5. ለባለብዙ ደረጃ የጥቃት መከላከያ ንቁ የደህንነት መፍትሄን መጫን/Install a proactive security solution for multi-layered protection

6. የምትክ ስርዓት መፍጠር /Back up your system/

7. መደበኛ አካውንት መጠቀም/ Use a standard user account/

8. የተጠቃሚ መለያ ቁጥጥርዎን ንቁ ማድረግ/Keep your User Account Control enabled/ - የተጠቃሚ መለያ ቁጥጥር በኦፕሬቲንግ ሲስተም ላይ ያልተፈቀዱ ለውጦችን እንዳይኖሩ ያግዛል።

No comments:

Post a Comment

#Mobile Phone

ሞባይል ስልክ ከተፈጠረ 51ኛ ዓመቱን ያዘ የመጀመርያዉ ተንቀሳቃሽ ስልክ ባለአንቴና፤ ከ1 ኪሎ በላይ የሚመዝን እና 25 ሴንቲሜትር ርዝመት ያለው ነበር። የሞባይል ስልክ በሰዉ ኪስ እና ቦርሳ ተቀምጦ ማገልገል ከጀመረ...