Tuesday, October 3, 2023

🌐 Status ኮዶች ምንድናቸው?

  ዌብሳይት (ድህረ ገጽ) 🌐 ስትጠቀሙ የሚመጡላችሁ መልእቶችን (HTTP Status Codes) በሚመለከት አንዳንዶቹን መርጠን እናያለን።


👉 Status ኮዶች ምንድናቸው?


✅ በComputer Client (ኮምፒውተር ተጠቃሚ) እና Server (የተጠቃሚው ጥያቄዎች የሚመልስ ኮምፒውተር) መሃከል ላይ የሚፈጠሩ የስራ ክንውን አመላካች ቁጥሮች ናቸው።


✅ እነኚህ ቁጥሮች በ3ት ዲጂት የሚገለጹ ሲሆን ከ 100 እስከ 599 ያሉትን ቁጥሮች ያካትታል!


✅ ዋነኞቹ (በተለይ ከ 404 - 501 በተጠቃሚው (Client) ወይም Server መሃል በሚፈጠሩ ግድፈቶች የሚመነጩ ሲሆኑ ግድፈት አመልካች ኮዶች (Error Codes) ተብለው ይጠራሉ!


〽️ ድህረ ገጾች ስንጠቀም አዘውትረው ከሚከሰቱ ኮዶች ጥቂቶቹን እንመልከት!


🔰 102 Processing:-

- ወደ ሰርቨሩ የላክነው መልእክት ተቀባይነት ማግኘቱን አመላካች ኮድ!


🔰 200 OK:-

- ይሄ ኮድ ድረገጾች ስንጠቀም የፈልግነውን በአግባቡ መሰራቱን  ከሰርቨሩ የሚላክልን ኮድ ነው, ለኛ ባይታየንም


🔰 303 See other:-

- መልእክት የላክልነት ሰርቨር ምንፈልገውን መረጃ ከሌለው ማግኘት ምንችልበትን ሌላ ቦታ (ሰርቨር) ጠቋሚ ኮድ ነው !


🔰 404 Not Found:-

- አብዛኞቻችን አጋጥሞን ሊሆን የሚችለው ኮድ ነው።

ወደ ሰርቨሩ የላክነው መልእከት (የተጠቀምነው የURL አድራሻም ሊሆን ይችላል) ሰርቨሩ ሳይኖረው ሲቀር የሚፈጠር ነው!


🔰  503 Service unavailable:-

- ዌብሳይት ስንጠቀም ሰርቨሩ ቢዚ ሆኖ ወይም ለጥገና (Website Under construction) የሚመነጭ ኮድ እና የተፈጠረው የሰርቨር ችግር ግዝያዊ መሆኑ አመልካች ኮድ ነው!


📌 በአጠቃላይ Status ኮዶች በ 5 ይከፈላሉ! እያንዳንዱ ክፍል የራሱ የሆነ ትርጉም አለው!


✅ ኮድ 1xx (Informational Code): በብዛት ባንጠቅምባቸውም ሰርቨሮች በትክክል ስራቸውን እየሰሩ መሆናቸውን አመላካች ኮዶች ናቸው!


✅  ኮድ 2xx (Success Code): ሰርቨሩ ላይ የተሰሩ ስራዎች በትክክል ተሰርተው ወደ ተጠቃሚወ መመለሱን ማሳያ ኮዶች !

 

✅ ኮድ 3xx (Redirection Code): ሰርቨሩ የፈለግነውን ሪሶርስ ከሌለው ሌላ ቦታ ላይ እንድንፈልግ ሚጠቁምበት መንገድ!


✅  ኮድ 4xx (Client Error): ከዌብሳይቱ ተጠቃሚ የሚመነጩ ግድፈቶች አመላካች ኮድ!


✅  ኮድ 5xx (Server Error): ሰርቨሮች መስራት የሚጠበቅባቸውን ሳይሰሩ ሲቀሩ የሚታይ ኮድ!

No comments:

Post a Comment

#Mobile Phone

ሞባይል ስልክ ከተፈጠረ 51ኛ ዓመቱን ያዘ የመጀመርያዉ ተንቀሳቃሽ ስልክ ባለአንቴና፤ ከ1 ኪሎ በላይ የሚመዝን እና 25 ሴንቲሜትር ርዝመት ያለው ነበር። የሞባይል ስልክ በሰዉ ኪስ እና ቦርሳ ተቀምጦ ማገልገል ከጀመረ...