ሞባይል ስልክ ከተፈጠረ 51ኛ ዓመቱን ያዘ
የመጀመርያዉ ተንቀሳቃሽ ስልክ ባለአንቴና፤ ከ1 ኪሎ በላይ የሚመዝን እና 25 ሴንቲሜትር ርዝመት ያለው ነበር።
የሞባይል ስልክ በሰዉ ኪስ እና ቦርሳ ተቀምጦ ማገልገል ከጀመረ 51 ዓመት ደፈነ። እንደ ጎርጎረሳዉያኑ አቆጣጠር በ1973 የሞቶሮላ መሐንዲስ ማርቲን ኩፐር የሞባይል ስልክን ለመጀመሪያ ጊዜ ለሕዝብ ያስተዋወቀ ጠበብት ነዉ።
አሜሪካዊዉ መሐንዲስ በዚያን ጊዜ ዓለም ያስተዋወቀዉ ተንቀሳቃሽ ስልክ ባለአንቴና፤ ከአንድ ኪሎ በላይ የሚመዝን እና 25 ሴንቲሜትር ርዝመት ያለው ነበር። በዚያን ጊዜ በዚህ ግዙፍ ተንቀሳቃሽ ስልክ 25 ደቂቃ ያህል ብቻ ነበር መነጋገር የሚቻለዉ። አሜሪካዊዉ የተንቀሳቃሽ ስልክ ፈጣሪ ዛሬ የ 95 ዓመት ባለፀጋ ነዉ። በዚህ 51 ዓመታት የሞባይል ስልክ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ፤ በረቀቀ እና በተሻለ ዘዴ ለሰዉ ልጅ አስፈላጊ ከሚባሉ ቁሳቁሶች መካከል ቀዳሚዉ ቦታ ይዞ እዚህ ደርሷል። በተንቀሳቃሽ ስልክ፤ ከተለያዩ ክፍለ ዓለማት ከመቅስበት የሚደርሱ ዜናዎችን ማንበብ፣ ፎቶዎችን ማንሳት፣ ኢሜሎችን መላክ እና በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መረጃዎችን መለጠፍ ለብዙ ተጠቃሚዎች የተለመደ ነገር ሆኗል። ዓለም ዛሬ ያለ ተንቀሳቃሽ ስልክ አይመሽለት አይነጋለት ሆኗል።
ለመሆኑ ተንቀሳቃሽ ስልክ ከመምጣቱ በፊት ኑሮው እንዴት ነው የነበር?
https://t.me/Computer_Android_tricks
Monday, April 8, 2024
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
#Mobile Phone
ሞባይል ስልክ ከተፈጠረ 51ኛ ዓመቱን ያዘ የመጀመርያዉ ተንቀሳቃሽ ስልክ ባለአንቴና፤ ከ1 ኪሎ በላይ የሚመዝን እና 25 ሴንቲሜትር ርዝመት ያለው ነበር። የሞባይል ስልክ በሰዉ ኪስ እና ቦርሳ ተቀምጦ ማገልገል ከጀመረ...

-
#windows_11 የዊንዶውስ 10 ኦፐሬቲንግ ሲስተም ይተካል ተብሎ የታሰበው አዲሱ የዊንዶውስ 11 ኦፐሬቲንግ ሲስተም ይፋ ሁኖል በጣም ብዙ አዳዲስ እና ማራኪ ነገሮዎችን ይዞ የቀረበው ይህ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ሰኔ(ጁ...
-
ቴሌግራም ፕሪሚየም ( Telegram Premium ) ምንድን ነው? በማኅበራዊ ሚዲያው የሰዎችን ትክክለኛ ገጽ ለማሳየት ከሚጠቅሙ ምልክቶች አንዱ የነበረው የማረጋገጫ ምልክት (Verification Badges ✅️) የነበር...
-
✳️ OpenAI ChatGPT ምንም መመዝገብ ሳያስፈልገው ቀጥታ ወደ ዌብሳይቱ እንደገባን ለመጠቀም ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል። 🔺ይህ እርምጃ የ AI ቴክኖሎጂዎችን ብዙዎች ጋር ተደራሽ የማድረግ ተልእኮ አካል ነው ተብሏል።...
No comments:
Post a Comment