Thursday, October 12, 2023

ቴሌግራም ፕሪሚየም ( Telegram Premium ) ምንድን ነው?

 


ቴሌግራም ፕሪሚየም ( Telegram Premium ) ምንድን ነው?

በማኅበራዊ ሚዲያው የሰዎችን ትክክለኛ ገጽ ለማሳየት ከሚጠቅሙ ምልክቶች አንዱ የነበረው የማረጋገጫ ምልክት (Verification Badges ✅️) የነበር ቢሆንም አሁን ላይ ግን ይህ ነገር ተለውጧል።


አሁን ላይ የማረጋገጫ ምልክቶችን በቀላሉ በገንዘብ መግዛት ስለሚቻል በስፋት ተአማኒነት ለማግኘት የሚፈልጉና ለማጭበርበር የሚያቅዱ ሰዎች የማሳመኛ መንገድ እየሆነም ይገኛል።


በተለይ የቴሌግራም የፕሪሚየም አገልግሎት ከዚህ ቀደም በፌስቡክና በሌሎች ማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከነበረው በአሰራሩም ሆነ በዓላማው የሚለይ ነው።


ዋና ዓላማው ምንድን ነው?

የቴሌግራም መተግበሪያ ገቢ ለማግኘት ካቀዳቸው ስልቶች መካከል አንዱ ይህ የፕሪሚየም አገልግሎት ነው። በመሆኑም ተጠቃሚዎች በመደበኛው አገልግሎት ከሚያገኙት ተጨማሪ አገልግሎቶችን በማቅረብ ለዛ አገልግሎት ክፍያ የሚጠይቅበት ሥርዓት ነው።


ይህ ሥርዓት ማንኛውም የቴሌግራም ተጠቃሚ መግዛት የሚችል ሲሆን በተጨማሪም በስጦታ መልክ ለሌሎች ሰዎች መግዛት ሁሉ ይቻላል።


በዚህ ጊዜ ቴሌግራም የግለሰቦችን ማንነት #የማያረጋግጥ ሲሆን ሰዎች በፈለጉት ስምና ማንነት ይህንን አገልግሎት አንዲያገኙ ያስችላቸዋል። በተጨማሪም በፈለጉት ጊዜና ወቅት ስማቸውን፣ የመለያ ሊንኩን (Username) #መቀየር ይችላሉ፤ ይህም ምንም ገደብ የለውም።


የቴሌግራም ፕሪሚየም ተጠቃሚዎች ምን የተለየ ነገር ያገኛሉ?

- መደበኛ ተጠቃሚዎች በቴሌግራም ከ2GB በላይ የሆነ ፋይል መላክ አይችሉም። የፕሪሚየም ተጠቃሚዎች በአንጻሩ እስከ 4GB ፋይል መላክ ይችላሉ።


- በቴሌግራም የተገደቡ አገልግሎቶችን በእጥፍ ለፕሪሚየም ተጠቃሚዎች ተፈቅዷል። ለአብነትም በመደበኛው መከታተል የምንችለው የቻናል ብዛት 500 ሲሆን በፕሪሚየም አገልግሎት እስከ 1000 ቻናሎችን መከታተል እንችላለን። ረጃጅም ጹሑፎችን ማቅረብም ለፕሪሚየም ተጠቃሚዎች የቀረበ ነው።


- የፕሪሚየም ተጠቃሚዎች ባጅ ይሰጣቸዋል። ይህ ባጅም የተለያዩ ስቲከሮችን መጠቀም የሚቻል ሲሆን መቀያየርም ይቻላል። በተጨማሪም ከመደበኛው ተጠቃሚዎች የተለየ ስቲከሮችን መጠቀም ይችላሉ።


የቴሌግራም የፕሪሚየም ተጠቃሚዎች ባጅ የማረጋገጫ ባጅ መሆን ይችላል?

🙅 አጭሩ መልስ አይሆንም የሚለው ነው። ይህ ምልክት ተጠቃሚዎች ከፍለው ተጨማሪ አገልግሎቶችን እያገኙ መሆኑን የሚያሳይ እንጂ የግለሰብን ትክክለኛ ማንነት የሚያረጋግጥ አይደለም።


ለዚህም ነው ማጭበርበር የሚፈልጉ ሰዎች የሌሎች ሰዎች ስምና ፎቶ በመጠቀም ለማሳመንና ሰዎችን ለማታለል የሚጠቀሙበት።

No comments:

Post a Comment

#Mobile Phone

ሞባይል ስልክ ከተፈጠረ 51ኛ ዓመቱን ያዘ የመጀመርያዉ ተንቀሳቃሽ ስልክ ባለአንቴና፤ ከ1 ኪሎ በላይ የሚመዝን እና 25 ሴንቲሜትር ርዝመት ያለው ነበር። የሞባይል ስልክ በሰዉ ኪስ እና ቦርሳ ተቀምጦ ማገልገል ከጀመረ...