Tuesday, October 3, 2023

ተደጋጋሚ የሞባይል ስልክ ችግሮች እና መፍትሔዎች

 

ተደጋጋሚ የሞባይል ስልክ ችግሮች እና መፍትሔዎች

#1.ለሌላ ሰዉ ድምጽ ይሰማል፡፡ ነገር ግን በጣም አነስተኛ ሲሆን ወይም የራቀ ድምጽ ሲሆን 909 ወይም 904 መደወል ጥሪዉ ሲጀምር የድምፅ መጨመሪያ ቁልፍን በመጫን ድምጹን  መጨመር ችግሩ ካልተፈታ ስፒከር ቀዳዳን ማፅዳት ከላይ በተገለጡት መንገዶች ካልተፈታ ስፒከሩን መቀየር ይኖርብናል፡፡


#2.የስልካችን ጥሪ ከተወሰኑ ሰከንዶች ወይም ደቂቃዎች በኋላ  ይቋረጣል፡፡ የስልካችን የጥሪ መቼት ላይ የጥሪ ገደብ /ኮል ታይም ሊሚት/Call time limit/ የሚለውን ማጥፍት በተለይ ቻይና ስልክ ላይ auto quick end የሚል መቼትን ማጥፍት፡፡

👉call record

👉General call setting

👉More

👉Auto quick -end

👉Off



#3.የቻይና ስልኮች ላይ ኪፓዱ ላይ ያለዉ ብርሀን ይታያል፣ በተጨማሪም ስክሪኑ ላይ ምስሎች ይታያሉ፡፡ ነገር ግን የስክሪኑ ብርሀን የማይታይ ከሆነ

ሁሉም የቻይና ስልኮች ስክሪናቸዉ ላይ ሶስት፣ አራት ወይም አምስት የስክሪን ዳዩድ መስመሮች ይገኛሉ፡፡ እነኝህ መስመሮች ከስክሪኑ ጋር የተበየዱበት ሊድ ሊለቅ ወይም ስክሪኑ ከቦርዱ ጋር የተበየደበት ቦታ ላይ የስክሪን ብርሀን መስመሮች ተላቀዉ ከሆነ በድጋሜ ፔስትና ሊድ በመጠቀም እያንዳንዱን እግር በአግባቡ መበየድ፡፡


#4.Insert SIM የሚል ጥሁፍ የሚያሳይ ከሆነ ሲም ካርዱ የሚሰራ መሆን አለመሆኑን የሚሰራ ስልክ በመጠቀም ማየት የሲም መርገጫ ብረቱን በእጃችን መጫን ሲም ኮኔክተሩን በቲነር ማጠብ እንደ 1110,6030,2600,2610,2310,1600 ያሉ ኖኪያ ስልኮች ላይ የሚሰራ ሲም ተጠቅመን Insert

Sim የሚል ጥሁፍ የሚያሳይ ከሆነ ቻርጅ ኮኔክተሩን ማፅዳት ወይም መቀየር ቻርጅ ኢንተርፌስ አካባቢ በቲነር ማፅዳት


#5.ባትሪ ሲገባበት ቫይብሬተር የሚያደርግ ከሆነ / ስልኩን ሳናበራዉ ልክ ባትሪ እንደገባበት በራሱ ቫይብሬት የሚያደርግ ከሆነ/ DCT3 ስልክ ከሆነ ዩአይ አይሲን መቀየር ሌሎች ስልኮች ላይ ፓወር አይሲ መቀየር


 #6.ኔት ወርክ የሌለው ስልክ አንቴና ኢንተርፌስ ወይም ከቦርዱ ጋር በአግባቡ መግጠሙን ማረጋገጥ ቦርዱን በቲነር ማጠብ አንቴና ስዊቹን ማሞቅ ኔትወርኩ አሁንም ካልተስተካከለ ደግሞ አንቴና ስዊች መቀየር


 #7.እኔ የምናገረው ይሰማል ሌላ ሰዉ የሚናገረዉ አይሰማኝም ስፒከሩን መቀየር



#8.ሰዉ የሚያወራው የሚሰማ ከሆነ ነገር ግን እኛ የምናወራው የማይሰማ ከሆነ ማይኩን መቀየር


#9.ወጭ ጥሪ ያደርጋል ነገር ግን አይቀበልም ኮል ዳይቨርት በርቶ ከሆነ ማጥፍት


#10.ከቁጥሮቹ መካከል አንዱ ብቻ ተነጥሎ የማይሰራ ከሆነ ቁጥሩ ላይ የሚያርፈዉን አልሙኒየም ማፅዳት


#11.ተንሸራታች ስልክ ላይ ያሉት ቁልፎች አይሰሩም ፣ከታች ያሉት ቁጥሮች በሙሉ ይሰራሉ

ኬብል መቀየር


 #12.የምን ሰማዉ ድምጽ ይንጫጫል/ ከሌላ ሰዉ ጋር ስንነጋገር/ ስፒከር መቀየር


#13.ቁጥሮች መደዳ የማይሰሩ ከሆነ ኪፓድ አይሲን ማሞቅ ወይም መቀየር


 #14.ስልኩ ክፍለሃገር ሲሄድ ኔትወርኩ አይሰራም ኔትወርክ ፊልተሩን መቀየር


#15.ስልክ ስናወራ የቁልፍ መጫን ድምፅ ይሰማናል/ ሳንነካዉ በራሱ ቁጥር ይደረድራል/ ኪፓድ አይሲን መቀየር


#16. ኔትወርክ ሙሉ ሁኖ ልክ ስንደዉል ኔትወርኩ ዜሮ ይሆናል ፓወር አምፕሊፋየሩን ማሞቅ ወይም መቀር

No comments:

Post a Comment

#Mobile Phone

ሞባይል ስልክ ከተፈጠረ 51ኛ ዓመቱን ያዘ የመጀመርያዉ ተንቀሳቃሽ ስልክ ባለአንቴና፤ ከ1 ኪሎ በላይ የሚመዝን እና 25 ሴንቲሜትር ርዝመት ያለው ነበር። የሞባይል ስልክ በሰዉ ኪስ እና ቦርሳ ተቀምጦ ማገልገል ከጀመረ...