#Gmail_የሚሰጣቸው_ጥቅሞች ያውቃሉ ??
#Gmail ማለት ጎግል ከሚሰጣቸው ከ 50 በላይ አገልግሎቶች አንዱ የመልእክት ወይም የኢሜል መለዋወጫ አገልግሎት ነው፡፡
#Gmail ኢሜል በምትላላኩበት ግዜ ብዙ አማራጮችን ይሰጣል፡፡ በተለይ አፕዴት ካደረጋችሁት፡፡
#Gmail ከሚሰጣቸው የተለያዩ ጠቀሜታዎች መካከል የተወሰኑትን ላንሳላችሁ፦
1ኛ፦ #Google_Smart_Compose_Feature
አንዳንዴ ኢሜል እየፃፋችሁ ቀጥሎ የምትፅፉትን ዓ/ነገር ወይም ሃሳብ ሲጠፋባችሁ ጎግል ይረዳችሃል፡፡
Google Smart Compose Feature የሚል አገልግሎት እዛወ ጂሜል ላይ ታገኛላችሁ፡፡ ይህ አገልግሎት ዓ/ነገር ሲጠፋባችሁ ወይም ሃሳብ ሲጠፋባችሁ "እንዲህ ማለት ፈልገህ ነው " እያለ ቀጥሎ ሊመጣ የሚችለውን ዓ/ነገር ገምቶ ይሞላላችኃል፡፡
2ኛ፦ #Schedule_emails_to_be_sent_at_a_later_date
ይሄ አገልግሎት ደሞ ለምሳሌ ከ 3 ቀናት በኃላ መላክ ያለባችሁ ኢሜል ካለና ነገር ግን በዛ ቀን ኢሜል ለመላክ የማይመቻቸሁ ከሆነ ለምሳሌ ሰርግ ቢኖርባችሁ ወይም ሌላ ነገር ቢኖርባችሁ ኢሜሉን ዛሬ ትፅፉትና ከሶስት ቀን በኃላ ለምሳሌ፡ቀኑ ሀሙስ በ12 ሰዓት ኢሜሉ ኢንዲላክ ስኬጁል ወይም ቀጠሮ ማስያዝ ይቻላል፡፡
3ኛ፦ ጂሜል ኢንተርኔት በማታገኙበት ጊዜ ወይም ኦፍ ላይን ስትሆኑም ጂሜልን መጠቀም ትችላላችሁ።
4ኛ፦ #Confidential_Mode: -
ይህ በጣም ጠቃሚ የጂሜል አገልግሎት ነው፡፡
ለምሳሌ፡- የቢዝነስ ፕሮፖዛል፣ወይም የፊልም ድርሰት፣ወይም በአጠቃላይ ሚስጥራዊ መረጃዎች በኢሜል ልትልኩ ስትሉ ትሰጋላችሁ። ምክንያቱም የምትሉክት ሚስጥራዎ መረጃ የላካችሁለት ሰው ቢወስድብኝስ፣ወይም ፕሪንት አድርጎ ቢጠቀምበትስ፣ወይም ዶክመቱን ማየት ለሌለበት ሰው ቢሰጥብኝብስ..ወዘተ የሚል ስጋት ይኖራችኃል፡፡
ነገር ግን ጂሜል ላይ Confidential Mode ኦን ካረጋችሁ ሚስጥራዊ መረጃ የላካችሁለት ሰው ዶክምንቱን ፕሪንት ማድረግ አይችልም፤ ኮፒ ማድረግ አይችልም፣ወደሌላ ሰው ኢሜል አድራሻም ፎርዋርድ ማድረግ አይችልም፡፡
5ኛ፦የጎግል አካውንት ወይም የጂሜል አካውንት ስትከፍቱ ጎግል 15 GB Space ይሰጣችኃል፡፡
ምንማለት ነው፦ስልካችሁ ላይ የምትፈልጓቸው ፎቶዎች፤ቪዲዮዎች፤ዶክመንቶች ይኖራሉ፡፡እነዚህንና የመሳሰሉ ጠቃሚ ዶክምንቶችን የምታስቀምጡበት 15 GB የሚሆን መጋዘን ይሰጣችኃል፡፡ በነፃ እዚህ ማስቀመጥ ትችላላችሁ፡፡፤ ሰዎች ስልኬ ጠፋ…እኔ ስልኩ ይቅርብኝ ግን ስልኩ ውስጥ ያሉ ዶክመንቶች መጥፋታቸው ነው የሚያናድደኝ ይላሉ፡፡ ካሁን በኃላ ጂሜል አካውንት ከከፈታችሁ ከዚያ ዶክመንቶቻችሁን ወደ ጂሜል ሲንክ ማድረግ ነው፡፡ጂሜል አካውንት ካላችሁ ስልካችሁ ሲሰረቅ ሌላ ስልክ ስትገዙ ጂሜላችሁን ከፍታችሁ ሁሉም ዶክመንቶቻችሁን ማግኘት ትችላላችሁ።
ሌላው ሰዎች ስልክ ሲጠፋባቸው ስልካቸው ላይ ያሉት ኮንታክቶች አብሮ ይጠፋሉ፡፡ እና ብዙ ሰው ይቸገራል ።፡ ስልካችሁ ቢጠፋም ጂሜል አካውንት ካላችሁ እያንዳንዱ ኮንታክቶቻችሁ ጂሜል ላይ ማግኘት ትችላላችሁ።
ሁላችሁም የ Gmail አካውንት ዛሬውኑ ማውጣት አለባችሁ፡፡
No comments:
Post a Comment