✳️ የዌብሳይት አድራሻ ክፍሎች
አንድ ዌብሳይት አድራሻ አራት የተለያዩ ክፍሎች አሉት።
ለምሳሌ፦ https://facebook.com/TechZone
የዚህ ዌብሳይት አድራሻ 4 ክፍሎች እንያቸው።
1ኛ፦ https ይህ ክፍል Scheme ይባላል
2ኛ፦facebook ይህ ክፍል Second Level Domain ይባላል
3ኛ፦ com ይህ ክፍል Top-Level-Domain ይባላል
4ኛ፦Tvdotcomshow Subdirectory ይባላል
እነዚህ አራት ክፍሎች እያንዳንዳቸው ትርጉም እና የሚሰሩት ስራ አላቸው።ነገርግን ዛሬ ልነግራችሁ የፈለኩት ስለ 3ኛው ክፍል(com) ነው።
የተለያዩ ኩባንያዎች ዌብሳይት አድራሻ ይኖራቸዋል።እነዚህ የተለያዩ ኩባንያዎች በተለያዩ ስራዎች ላይ የተሰማሩ ሊሆኑ ይችላሉ።
አንድ ዌብሳይት አድራሻን በማየት ብቻ የዌብሳይቱ ባለቤት የሆነው ኩባንያ በምን ዓይነት ስራ ላይ እንደተሰማራ ማወቅ ይቻላል።ይህንን መረጃ የሚሰጠን የዌብሳይቱ አድራሻ 3ኛው ክፍል ነው።
ይህ ክፍል( Top-Level-Domain )የተለያዩ ዌብሳይት አድራሻ ውስጥ 3 ፊደላት ቅጥያ የያዘው ክፍል ሲሆን የተለያዩ ኩባንያዎች የተሰማሩበት ዘርፍ የሚጠቁሙ የተለያዩ ባለ 3 ፊደላት ቅጥያዎች ያላቸው የዌብሳይት አድራሻዎች ላይ እናገኛለን።
ከነዚህ ባለ 3 ፊደላት ቅጥያዎች መካከል ለምሳሌ፦ .edu፣.gov፣.com፣.net፣.info፣net ወዘተ መጥቀስ ይቻላል።
እነዚህ ባለ 3 ፊደላት ቅጥያዎች ስለኩባንያዎቹ የሚነግሩንን ትርጉሞች እንመልከት።
1ኛ፦ .com ይህ ቅጥያ ያለው ዌብሳይት አድራሻ ማለት ኩባንያው በንግድ ላይ የተሰማራ ኩባንያ ነው ማለት ነው።
com ማለት Commercial ለማለት ነው።
2ኛ፦.net ይህ ቅጥያ ያለው ዌብሳይት አድራሻ ማለት ኩባንያው የቴሌኮሙኒኬሽን ወይም የቴክኖሎጂ ተቋም ነው ማለት ነው።
net ማለት Network ለማለት ነው።
3ኛ፦.gov ይህ ቅጥያ ያለው ዌብሳይት አድራሻ ማለት ኩባንያው መንግስታዊ ተቋም ነው ማለት ነው።
gov ማለት Government ለማለት ነው።
4ኛ፦.info ይህ ቅጥያ ያለው ዌብሳይት አድራሻ ማለት ኩባንያው መረጃ የሚያሰራጭ ተቋም ነው ማለት ነው።
info ማለት Information ማለት ነው።
5ኛ፦ .edu ይህ ቅጥያ ያለው ዌብሳይት አድራሻ ማለት ኩባንያው የቴትምህርት ተቋም ነው ማለት ነው።ለምሳሌ ዩኒቨርሲቲዎች።
edu ማለት Education ማለት ነው።
6ኛ፦.biz ይህ ቅጥያ ያለው ዌብሳይት አድራሻ ማለት ኩባንያው የቢዝነስ ተቋም ነው ማለት ነው።
biz ማለት Business እንደማለት ነው።
No comments:
Post a Comment