Sunday, October 1, 2023

የሞባይል ባንኪንግ ሲጠቀሙ ሊያደርጓቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎች

 ✳️ የሞባይል ባንኪንግ ሲጠቀሙ ሊያደርጓቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎች



🚩የሞባይል ባንኪንግ የባንክ አገልግሎቶችን ወደ ባንኮች ቅርንጫፍ መሄድ ሳያስፈልግ በተንቀሳቃሽ ስልኮች አማካኝነት ብቻ የባንክ አገልግሎቶችን ማለትም ገንዘብ መላክ እና መቀበል እንዲሁም የተለያዩ ክፍያዎችን ለመፈፀም የሚያስችል ቴክኖሎጂ ነው፡፡


🚩የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት የተጠቃሚዎችን ድካም ከመቀነስ ጋር በተያያዘ አገልግሎቱን ተመራጭና ቀላል ያደርገዋል፤ ታዲያ ይህ አገልግሎት የቴክኖሎጂ ውጤት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ተጓዳኝ የመረጃ መረብ ጥቃት ተጋላጭነት አያጣውም፡፡


🚩ተጠቃሚዎች አገልግሎቱን ሲጠቀሙ የሚከተሉትን ጉዳዮች ሊያውቋቸው እና ጥንቃቄ ሊያደርጉባቸው ይገባል ሲል የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ይመክራል፡፡


➊. የተረጋገጡና ትክክለኛ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያዎችን (application) ከተረጋገጡ ምንጮች አውርዶ መጠቀም፦ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያዎች ትክክለኛ በባንኩ እውቅና ያላቸው መሆኑንና የሚገኙትም በትክክለኛው የመተግበሪያ ቋት ማለትም ለአንድሮይድ የመተግበሪያ ቋት ወይም ለአይ.ኦ.ኤስ ኦፕሬቲንግ ሲስተም በማውረድ መጠቀም ተገቢ ነዉ፡፡


➋. በስልኮች ላይ ያሉ ሌሎች መተግበሪያዎች ፍቃዶችን ማጥናት፡- በስልክዎ ላይ የሚገኙ ሌሎች መተግበሪያዎች የሚጠይቋቸውን ግንኙነቶች (አክሰስ) ልብ ይበሉ፡፡

መተግበሪያዎች ለአገልግሎቶቻቸው ከሚያስፈልጋቸው የሞባይል መረጃ ዉጪ ሌሎች መረጃዎች እንዲዳረሱ እንዳይፈቅዱ፡፡


➌. አፕሊኬሽኖችን /መተግበሪያዎችን ማዘመን፡- በስልኮች ላይ የሚገኙ የባንኪንግ መጠቀሚያ መተግበሪያዎችን ወቅቱን ጠብቀዉ ያዘምኑ፡፡

መተግበሪያዎች ላይ ለስርቆት የሚዳርጋቸው ክፍተቶች ሲገኙ በየወቅቱ ማዘመኛ ስለሚለቀቅላቸው የደህንነት ክፍተቶቹን ለመድፈንና የባንክ ሂሳብዎን ደህንነት ለማስጠበቅ በየጊዜው ያዘምኗቸው፡፡


➍. የሞባይል ስልክ ኦፕሬቲንግ ሲስተምን ማዘመን፡- የስልክዎን ደህንነት ክፍተት ለመሙላት በየጊዜው ክፍተት መሙያና ማሻሻያ እድሳቶች ስለሚለቀቁ በየወቅቱ እየተከታተሉ ያዘምኗቸው፡፡


➎. ከህዝብ መገልገያ ዋይፋይ ይልቅ የሞባይል ዳታ ይጠቀሙ፡- የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎቶችን በሞባይልዎ ለመጠቀም ለህዝብ መገልገያ የቀረቡ ነፃ ዋይፋዮችን ከመጠቀም ይልቅ የሞባይል ዳታዎችን ይጠቀሙ፡፡


➏. ዘርፈ-ብዙ የደህንነት ማስጠበቂያ የይለፍ-ቃሎችን ይጠቀሙ፦ ሞባይል ስልክዎን በአሻራ፣ ፊት ማንበብያ (ፌስ ሪኮግኒሽን)፣ ፓተርን፣ ፓስወርድ እና ፓስ ኮድ የመሳሰሉትን በመጠቀም ስልክዎን ይቆልፉ፡፡


➐. በማህበራዊ ሚዲያ የሚለቋቸውን ግላዊ መረጃዎች ይገድቡ፡- በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚለቀቁ መረጃዎች የተገደቡ ሊሆኑ ይገባል፡፡


➑. ፀረ-ቫይረስ (ማልዌር) ይጠቀሙ


➒. የሞባይል ስልክዎን አካላዊ ደህንነት ያስጠብቁ


➓. የባንክ ሂሳብዎን ዘወትር ይከታተሉ፡- በተጨማሪ ተገቢውን ሁሉ ጥናቃቄ ካደረጉ በኋላም ስለ ባንክ አካውንትዎ የሚደርሱ ማንቂያዎችን (notifications) በአግባቡ መከታተል እንዲሁም በየጊዜው ስለ አካውንትዎ ሁናቴ (ስታተስ) መከታተል እና የማያውቁት የሂሳብ ለውጥ ካለ በአፋጣኝ ለባንክዎ ያሳውቁ፡፡



No comments:

Post a Comment

#Mobile Phone

ሞባይል ስልክ ከተፈጠረ 51ኛ ዓመቱን ያዘ የመጀመርያዉ ተንቀሳቃሽ ስልክ ባለአንቴና፤ ከ1 ኪሎ በላይ የሚመዝን እና 25 ሴንቲሜትር ርዝመት ያለው ነበር። የሞባይል ስልክ በሰዉ ኪስ እና ቦርሳ ተቀምጦ ማገልገል ከጀመረ...