Friday, September 29, 2023

SSD and HDD ምንድንነው ልዩነታቸው?


                         SSD and HDD ምንድንነው ልዩነታቸው ?

✅ SSD ማለት Solid State Drive ማለት ሲሆነ HDD ማለት Hard Disk Drive ማለት ነው።


✅ HDD አሁን ካለው የቴክኖሎጂ ሁኔታ የድሮ ቴክኖሎጂ እየተባ የሚጠራ ሲሆን አሁን ላይ ይህንን ቴክኖሎጂ ሁሉም የኮምፒውተር አምራች ድርጅቶች Hard disk Drive መጠቀምን በማቆም ላይ ናቸው።


✅ SSD Solid State Drive አሁን ላይ HDD በመተካት አዲስ የመረጃ ማከማቻ ቴክኖሎጂ እየሆነ ነው። አሁን ላይ ሁሉም የኮምፒውተር አምራች ድርጅቶች የመረጃ ማከማቻ ቴክኖሎጂን ከHDD በላይ SSD እየተጠቀሙ ይገኛሉ።


✅ HDD ኤችዲዲ ወይም ሃርድ ዲስክ ከመግነጢሳዊ ቴፕ የተሰራ እና በውስጡም ሜካኒካል ክፍሎችን የያዘ የመረጃ ማከማቻ መሳሪያ ነው። 


✅ HDD መረጃን ለማንበብ(Read) እና ለመፃፍ(Write) በሚሽከረከር ዲስክ ወይም በብረት ፕላስተር ማግኔቲክ የተሸፈነ ነው። 


✅ HDD መረጃውን ለማንበብና ለመጻፍ ዲስኩን የሚያሽከረክረው ሞተር ሲኖረው ዲስኩ ሲሽከረከር አንባቢ እጀታ ተገጥሞለታል።


✅ ለHDD ላፕቶፖች  2.5 ኢንች መጠን ያላቸው ሲሆን  ለዴስክቶፕ  ኮምፒውተሮች  3.5 ኢንች ነው። 

HDD በብዛት SATA («stands for "Serial Advanced Technology Attachment," or "Serial ATA") ኢንተርፊስን ይጠቀማሉ።


✅ SDD ከHDS ጋር አንድ አይነት ተግባራትን ያከናውናል፣ ነገር ግን SDD መረጃን ለማከማቸት interconnected flash-memory chips (እርስ በርስ የተያያዙ ፍላሽ-ሜሞሪ ቺፖችን) ይጠቀማሉ።


✅ ስሙ እንደሚያመለክተው solid-state drive ፣ ይህ ማለት በSSD ውስጥ ምንም ተንቀሳቃሽ ክፍሎች የሉም ወይም እንደ HDD የሚሽከረከር ዲስክ የለም። 


✅ SSD ከSATA Ports እና 2.5 ኢንች ፎርማት በHDS ምትክ በቀላሉ ከኮምፒውተር ጋር ማገናኘት ይቻላል።


✅ እንዲሁም በሚኒ-PCI (Peripheral Component Interconnect) ኤክስፕረስ ማስገቢያዎች ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውሉ ሚኒ-SATA (mSATA) ያላቸው ትናንሽ SSDs አሉ። 


✅ አብዛኞቹ ዘመናዊ ላፕቶፖች SSD በ PCI Express Expansion slot  ከገባ ወይም በቀጥታ በማዘርቦርድ ላይ በማገናኘት መጠቀም ይቻላል። 


✅ HDD ከSSD ርካሽ ነው

✅ HDD ከSSD ዝቅተኛ የሆነ መረጃን Read/Write የማድረግ አቅም አለው

✅ HDD ከSSD በይበልጥ ሀይል(ባትሪ) ይጠቀማል

✅ HDD ከSSD ዲስኩ ስለሚሽከረከር ድምጽ የማሰማት ሁኔታ ይታያል

✅ HDD ከSSD በጥንካሬ/ በቆይታ የተሻለ ነው

✅ HDD ከSSD በክብደትና በአካላዊ ግዝፈት ይበልጣል 


⚠️ ኮምፒውተራችን SSD ወይም HDD Disk መሆኑን ለማርጋግጠ  የWindows key + R ቁልፍ ስትጫኑ Run box ይመጣል ከዛም, dfrgui በመጻፍ  Enter ይጫኑ.

Drive Media Type የሚል ቦክስ ይመጣል ከዛም የኮምፒውተር ዲስክ HDD ከሆነ Hard Disk Drive ወይም SSD ከሆነ Solid State Drive የሚል ይመጣል።


No comments:

Post a Comment

#Mobile Phone

ሞባይል ስልክ ከተፈጠረ 51ኛ ዓመቱን ያዘ የመጀመርያዉ ተንቀሳቃሽ ስልክ ባለአንቴና፤ ከ1 ኪሎ በላይ የሚመዝን እና 25 ሴንቲሜትር ርዝመት ያለው ነበር። የሞባይል ስልክ በሰዉ ኪስ እና ቦርሳ ተቀምጦ ማገልገል ከጀመረ...