አንድ ዌብሳይት ጥሩ ነው የምንለው ምን ምን ሲያካትት ነው?
ድርጅቶት ወይም የግል ዌብሳይቶ መኖሩ ብቻ ብዙ ላይጠቅም ይችላል። የዲጂታል መገኛዎ ውበት ከቢሮው ውበት እኩል ሊያስጨንቆት ይገባል። ይህንን ስንል አሁን ያለው የድርጅቶ ዌብሳይት (ወደፊት የሚያሰሩት) ጥሩ ነው ለመባል ቢያንስ በእነዚህ መመዘኛዎች ተፈትኖ ማለፍ አለበት።
1. ምክንያታዊነት
ዌብሳይቱ ለምንድነው ያስፈለገው? አላማው ምንድነው? ማን ይመለከትልኛል? ምን መግለጽ አለበት? የሚሉትን ጥያቄዎች በአግባቡ መመለስ አለበት። ይህ ካልሆነ በተመልካቹ ዘንድ ቅሬታ ይፈጥራል ለፍተውና ገንዘቦትን አውጥተው ያሰሩት ድረ ገጾ የሚፈለገውን ጥቅም ሳያስገኝ ይቀራል።
2. ለአጠቃቀም ቀላል
ዌብሳይቶ ለአጠቃቀም ቀላል መሆን ይጠበቅበታል። ደንበኛዎ የሚፈልገውን ነገር ሳይጨናነቅ፤ ሳይጉላላ በቀላሉ ማግኘት እንዲችል ተደርጎ መሰራት ይኖርበታል። ለአጠቃቀም ቀላል ዌብሳይት ማሰራት ጥሩ ባለሞያ የሚፈልግና ዋነኛ መመዘኛ ነው።
3. ይዘት
ዌብሳይቶ ምን መረጃ ይዟል? ስለድርጅቴ በአግባቡ ገልጾልኛል ወይ? ደንበኞቼ ስለ አገልግሎቴ በቀላሉ መረዳት ይችላሉ? የሚሉት ነገሮች መታሰብ ይኖርባቸዋል። የዲጂታል ይዘቶች እንደ ወረቀት ይዘቶች በጹሑፍ ብቻ ሳይሆን በግራፊክስ፤ በምስል፤ በኢንፎግራፊክስ የሚቀመጡ ጭምር ናቸው ይህም ተጠቃሚዎች በቀላሉ እንዲረዱ ያስችላቸዋል።
4. ፍጥነት
ዌብሳይቶ ሲዘገይ ከኔትወርክ ችግር ብቻ ከመሰሎት ተሳስተዋል። የተሰራበት ጥራትና የተጠቀማቸው የኮዲንግ መንገዶች ለዌብሳይቱ ፍጥነት እጅግ ወሳኝ ናቸው። ስለዚህ ሥራዎትን በጥሩ ባለሞያ ካሰሩ ይበልጥ ተጠቃሚ ይሆናሉ።
5. ተግባቦት
የተሰራው ዌብሳይት በኮምፒውተር ሲመለከቱት እንዲሁም በስልክና በታብሌት ሲመለከቱት በሦስቱም ላይ እንደቅርጻቸው ተግባብቶ ካልሰራ ዌብሳይቶ ጥሩ አልተሰራም ማለት ነው። በመሆኑም የድርጅቶ ዌብሳይት ከኮምፒውተር እንዲሁም ከስልክና ከታብሌት ተግባቢ መሆኑንን ማረጋገጥ ይጠበቅባችኋል።
6. በቀላሉ መገኘት (SEO)
ሰዎች በተለያዩ መንገድ አገልግሎት ሲፈልጉ የእርሶን ዌብሳይት በቀላሉ ማግኘት መቻል ይጠበቅባቸዋል። ለዚህ የሚያግዙ ቴክኒካል ጉዳዮች በአግባቡ መሰራት ይጠበቅበታል። ጥራት ያለው ዌብሳይት እንዳሎት ይህንንም ማረጋገጥ ይኖርቦታል።
7. ልዩ እና የሚታወስ
በጣም ስኬታማ የተባሉ ዌብሳይቶች ከሌሎች ልዩ የሚያደርጋቸውን ባህሪይ የያዙ ናቸው። የእርሶን ዌብሳይት ልዩ ለማድረግ በርካታ መንገዶችን መጠቀም ይችላሉ ለምሳሌ የዲዛይን ጥራት፣ ጥሩ ይዘት፣ ደረጃውን የጠበቀ ግራፊክስ፣ መረጃዎችና ጠቃሚ መሳሪያዎችን ማንሳት ይቻላል። የደንበኛዎትን ቀልብ ገዝተው መያዝ ከፈለጉ ዌብሳይቶ ሰዎች እነዲጎበኙት በቂ ምክንያት እንዲኖራቸው ማድረግ ይጠበቅቦታል።
8. ደኅንነቱ የተጠበቀ
በዚህ ዘመን የቢሮዎት ደኅንነት ብቻ ሳይሆን በበይነ መረብ ተጠቅመው የሚያካሂዱት እንቅስቃሴዎችም ደኅንነቱ የተጠበቀ መሆን ይጠበቅበታል። ለደንበኛዎም ሆነ የእርሶ ደኅንነት እንዲሁም መረጃ የሚያስጠብቅ ጥብቅ ድረገጽ ሊኖሮት ያሻል።
No comments:
Post a Comment