Monday, April 8, 2024

#Mobile Phone


ሞባይል ስልክ ከተፈጠረ 51ኛ ዓመቱን ያዘ የመጀመርያዉ ተንቀሳቃሽ ስልክ ባለአንቴና፤ ከ1 ኪሎ በላይ የሚመዝን እና 25 ሴንቲሜትር ርዝመት ያለው ነበር። የሞባይል ስልክ በሰዉ ኪስ እና ቦርሳ ተቀምጦ ማገልገል ከጀመረ 51 ዓመት ደፈነ። እንደ ጎርጎረሳዉያኑ አቆጣጠር በ1973 የሞቶሮላ መሐንዲስ ማርቲን ኩፐር የሞባይል ስልክን ለመጀመሪያ ጊዜ ለሕዝብ ያስተዋወቀ ጠበብት ነዉ። አሜሪካዊዉ መሐንዲስ በዚያን ጊዜ ዓለም ያስተዋወቀዉ ተንቀሳቃሽ ስልክ ባለአንቴና፤ ከአንድ ኪሎ በላይ የሚመዝን እና 25 ሴንቲሜትር ርዝመት ያለው ነበር። በዚያን ጊዜ በዚህ ግዙፍ ተንቀሳቃሽ ስልክ 25 ደቂቃ ያህል ብቻ ነበር መነጋገር የሚቻለዉ። አሜሪካዊዉ የተንቀሳቃሽ ስልክ ፈጣሪ ዛሬ የ 95 ዓመት ባለፀጋ ነዉ። በዚህ 51 ዓመታት የሞባይል ስልክ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ፤ በረቀቀ እና በተሻለ ዘዴ ለሰዉ ልጅ አስፈላጊ ከሚባሉ ቁሳቁሶች መካከል ቀዳሚዉ ቦታ ይዞ እዚህ ደርሷል። በተንቀሳቃሽ ስልክ፤ ከተለያዩ ክፍለ ዓለማት ከመቅስበት የሚደርሱ ዜናዎችን ማንበብ፣ ፎቶዎችን ማንሳት፣ ኢሜሎችን መላክ እና በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መረጃዎችን መለጠፍ ለብዙ ተጠቃሚዎች የተለመደ ነገር ሆኗል። ዓለም ዛሬ ያለ ተንቀሳቃሽ ስልክ አይመሽለት አይነጋለት ሆኗል። ለመሆኑ ተንቀሳቃሽ ስልክ ከመምጣቱ በፊት ኑሮው እንዴት ነው የነበር? https://t.me/Computer_Android_tricks

ቴሌግራም የቢዝነስ ሶሻል ሚዲያነት እየተቀየረ እንደሆነ ይታወቃል።









ቴሌግራም በዚህ አመት ካስተዋወቃቸው ፊቸሮች መካከል አንዱ Telegram business ነው ። እነዚህ ፊቸርች ምን ምን እንደሆኑና ለምትጀምሩትን ቢዝነስ ምን ጠቀሜታ እንዳለው አንድ በአንድ ለማየት እንሞክር። ✅️Location: ቢዝነሳችሁን የምትሰሩበትን አካባቢ ሰዎች በቀላሉ እንዲውቁትና Google map ተጠቅመው እንዲመጡ ፕሮፋይላችሁ ላይ  መሙላት ትችላላችሁ። ✅️ Opening houre: ቢዝነሳችሁን የምትከፍቱበትና የምትዘጉበትን ሰአት ሰዎች በቀላሉ እንዲያውቁት ፕሮፋይላችሁ ላይ  መሙላት ትችላላችሁ። ✅️ Quick Replies: ብዙ ሰዎች Contact የሚያድርጓችሁ ከሆነና ለሁሉም ተመሳሳይ አይነት መልዕክት የምትልኩ ከሆነ ሁሉንም አንድ በአንድ መፃፍ ሳይጠበቅባችሁ በshortcut መላክ ትችላላችሁ። ✅️Greeting message: ሰዎች Contact ሲያደርጓችሁ የመጀመርያውን ቻት እናንተ መመለስ ሳይጠበቅባችሁ automatically በራሱ መልስ እንዲስጥ የምታደርጉበት ነው። ይህን ፊቸር ለመጠቀም የምትፈልጉትን ፅሁፍ አስቀድማችሁ መሙላት አለባችሁ። ✅️Away message: ለተወሰነ ጊዜ online የማትገቡና ለሰዎች መልስ መስጠት የማትችሉ ከሆነ ሰዎች contact ሲያደርጓችሁ መልሲ እንዲሰጥላችሁ የፈለጋችሁትን መልዕክት መሙላት ትችላላችሁ። ✅️Links to chat: አዳዲስ ሰዎች ቴሌግራም ላይ contact እንዲያደርጓችሁ ፈልጋችሁ ነገር ግን ዩሰርኔማችሁን ወይም ስልክ ቁጥራችሁን መስጠት ካልፈለጋችሁ ምንም ችግር የለም ይህን ፊቸር መጠቀም ትችላላችሁ።  የተለያዩ ሊንኮችን በመፍጠርና ሊንኩን ለሰዎች share በማድረግ ዩሰርኔማችሁንና ስልክ ቁጥራችሁን መስጠት ሳይጠበቅባችሁ inbox እንዲያደርጉላችሁ ማድረግ ትችላላችሁ። ✅️Custom Intro: ሰዎች ለመጀመርያ ጊዜ ሊፅፉላችሁ ቻቱን ሲከፍቱት የሚመጣውን ፅሁፍና sticker እንደተመቻችሁ edit ማድረግ ትችላላችሁ። ✅️ChatBots: ቦት ካላችሁ አካውንታችሁ ላይ በማካተት ለሰዎች automatically መልስ እንዲሰጥ ማድረግ ትችላላችሁ።

✳️ OpenAI ChatGPT

✳️ OpenAI ChatGPT ምንም መመዝገብ ሳያስፈልገው ቀጥታ ወደ ዌብሳይቱ እንደገባን ለመጠቀም ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል። 🔺ይህ እርምጃ የ AI ቴክኖሎጂዎችን ብዙዎች ጋር ተደራሽ የማድረግ ተልእኮ አካል ነው ተብሏል። https://chat.openai.com/ #Ai #OpenAI #ChatGPT

Telegram ክፍያ ሊጀምር ነው::

ቴሌግራም ቻናሎች ላይ ማስታወቂያዎችን ማስተላለፍ ሊጀምር ነው። ከነዚህ ማስታወቂያዎች የሚገኘው ገቢም ለቻናል ባለቤቶች ግማሽ የሚያካፍል ይሆናል። ለማስታወቂያው ብቁ የሚሆኑ public ቻናሎች ሲሆኑ ቢያንስ 1000 ሰብስክራይበሮች ሊኖራቸው ይገባል። ክፍያው የሚፈፀመው በTON coin ሲሆን ያለምንም ክፍያ ወደ ton ዋሌታቸው መላክና ማውጣት እንደሚችሉ ተገልጿል። የቻናሉን monetization states የቻናሉ owner channel settings > Statistics > minitization ውስጥ ገብቶ ማየት ይቻላል። ለመመዝገብና የሰራነውን ገንዘብ ለማየት 1. fragment.com ላይ መግባት 2. Connect Telegram የሚለውን በመምረጥ telegram አካውንታችንን connect ማድረግ 3. Telegram Ads የሚል አዲስ የተጨመረ ምርጫ አለ እሱን በመንካት ማስታወቂያ ማስነገር ወይም በቻናላችን የሰራነውን ማውጣት እንችላለን። የማስታወቂያው አይነት ከሌሎች ሶሻል ሚዲያዎች ለየት ያለ ሊሆን እንደሚችል ተገልጿል። ይህም በuser data ላይ መሰረት አያደርግም። ቪዲዮና ረዘም ያለ ፅሁፍ አይኖረውም። ፕሪምየም ቴሌግራም ያለው ሰው እነዚህን ማስታወቂያዎች አያይም። ማስታወቂያ የሚተላለፍባቸው ቻናሎች እንደሌሎች ሶሻል ሚዲያዎች የተለመደውን የኮፒራይት ህግን ማሟላት ይኖርባቸዋል። ቻናሉ ላይ የሚተላለፈው original content መሆን አለበት። ከሌሎች ቻናሎች ወይም ሲሻል ሚዲያዎች ቀጥታ የተገለበጡ ኮንቴንቶች monetize አይሆኑም። ወሲብ ነክ ይዘት ያላቸው፣ የተሳሳተ መረጃና የጥላቻ ንግግር የሚያስተላልፉ ቻናሎችም ለማስታወቂያ ብቁ አይሆኑም።

List Of United States of America Scholarships For International Students #bachelor #master #phd

List Of United States of America Scholarships For International Students #bachelor #master #phd ###Please share it with your networks 1. Boston University Scholarships Link: https://lnkd.in/dx4Xn7Z 2. University of Miami Stamps Scholarship Link: https://lnkd.in/dZQ_sKnR 3. Fulbright Foreign Student Scholarship 2023 Link: https://lnkd.in/gqEbbnqN 4. San Jose University Global Spartan Scholarship Link: https://lnkd.in/dFzMheyh 5. US Embassy YSEALI Academic Fellowships Link: https://lnkd.in/dYcN4_gM 6. Illinois Wesleyan University USA Scholarship Link: https://lnkd.in/dwri8MRT 7. Houston University Hawk Scholars Scholarship Link: https://lnkd.in/ggVzwxPZ 8. Chapman University Scholarship Link: https://lnkd.in/ddeXVhPn 9. Simmons University Kotzen Scholarship Link: https://lnkd.in/ggFwEJUK 10. The University of Michigan Scholarships Link: https://lnkd.in/gu_PiaaE

#የፀሀይ_ግርዶሽ

ዛሬ ሰኞ በተለያዩ ሀገራት ሙሉ የፀሀይ ግርዶሽ እየታየ ይገኛል። በተለይ በሜክሲኮ እና አሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች ሙሉ የፀሐይ ግርዶሽ እየታየ ነው። የተለያዩ ቦታዎች በፀሀይ ግርዶሹ ምክንያት ከ3 ደቂቃ ለበለጠ ጊዜ በሙሉ #ጨለማ_ተውጠው ታይተዋል። ክስተቱንም በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች እየተመለከቱት ነው። የፀሀይ ግርዶሽ #ጨረቃ በምድር እና በፀሀይ  መካከል ስታልፍ የፀሀይን እይታ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል በምትጋርድበት ጊዜ የሚከሰት ነው። 

#Mobile Phone

ሞባይል ስልክ ከተፈጠረ 51ኛ ዓመቱን ያዘ የመጀመርያዉ ተንቀሳቃሽ ስልክ ባለአንቴና፤ ከ1 ኪሎ በላይ የሚመዝን እና 25 ሴንቲሜትር ርዝመት ያለው ነበር። የሞባይል ስልክ በሰዉ ኪስ እና ቦርሳ ተቀምጦ ማገልገል ከጀመረ...